Ezekiel 30

ስለ ግብፅ የወጣ ሙሾ

1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ ‘ዋይ! በል፤ እንዲህም በል፤
“ወዮ ለዚያ ቀን!”
3ቀኑ ቅርብ ነው፤
የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤
የደመና ቀን፣
ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።
4በግብፅ ላይ ሰይፍ ይሆናል፤
በኢትዮጵያም ላይ ጭንቀት ይመጣል።
የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣
ሀብቷ ይወሰዳል፤
መሠረቶቿም ይፈርሳሉ።
5ኢትዮጵያና ፉጥ፣ ልድያና መላው ዐረብ፣ ሊብያና
ዕብራይስጡ ኩብ ይላል።
የቃል ኪዳኑ ምድር ሕዝብ ከግብፅ ጋር በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ።

6“ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ ‘የግብፅ ተባባሪዎች ይወድቃሉ።
የምትኵራራበት ብርታቷ ይወድቃል።
ከሚግዶል እስከ አስዋን፣
በውስጧ በሰይፍ ይወድቃሉ፤
ይላል ጌታ እግዚአብሔር
7በባድማ መሬቶች መካከል፣
ባድማ ይሆናሉ፤
ከተሞቻቸውም፣
ከፈራረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ።
8በግብፅ ላይ እሳት ስጭር፣
ረዳቶቿ ሁሉ ሲደቅቁ፣
በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
9“ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ተዘልላ ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብፅ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በርግጥ ይመጣልና።

10“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ ‘በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፣
ስፍር ቍጥር የሌለውን የግብፅን ሕዝብ እደመስሳለሁ።
11ከአሕዛብ ሁሉ እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እርሱና ሰራዊቱ፣
ምድሪቱን ለማጥፋት እንዲመጡ ይደረጋል፤
ሰይፋቸውን በግብፅ ላይ ይመዝዛሉ፤
ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ፤
12የአባይን ወንዝ ውሃ አደርቃለሁ፤
ምድሪቱን ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ፤
በባዕዳን እጅ፣ ምድሪቷንና በውስጧ
ያለውን ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤
እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።

13“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ ‘ጣዖታትን አጠፋለሁ፤
በሜምፊስ
ዕብራይስጡ ኖፍ ይለዋል፤ እንዲሁም በ16
ያሉትን ምስሎች እደመስሳለሁ።
ከእንግዲህ በግብፅ ገዥ አይኖርም፣
በምድሪቱም ላይ ፍርሀት እሰዳለሁ።
14ጳትሮስን ባድማ አደርጋለሁ፤
በጣኔዎስ ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤
በቴብስ
ዕብራይስጡ ይለዋል፤ እንዲሁም በ15 እና 16
ላይ ቅጣት አመጣለሁ።
15የግብፅ ምሽግ በሆነችው፣
በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፤
ስፍር ቍጥር የሌለውን የቴብስን ሕዝብ አጠፋለሁ።
16በግብፅ ላይ እሳት አነድዳለሁ፤
ሲን በጭንቅ ትናጣለች፤
ቴብስ በማዕበል ትወሰዳለች፤
ሜምፊስ በማያቋርጥ ጭንቀት ውስጥ ትገባለች።
17የሄልዮቱና
ዕብራይስጡ አዌን (ወይም ኦን) ይለዋል
የቡባስቱ
ዕብራይስጡ ፊ ቢሴት ይላል
ጕልማሶች፣
በሰይፍ ይወድቃሉ፤
ከተሞቹ ራሳቸውም ይማረካሉ።
18የግብፅን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ፣
በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤
ከዚያም የተኵራራችበት ብርታት ይንኰታኰታል።
በደመና ትሸፈናለች፤
መንደሮቿም ይማረካሉ።
19ስለዚህ በግብፅ ላይ ቅጣቴን አመጣለሁ፤
እነርሱም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
20በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር በሰባተኛው ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 21“የሰው ልጅ ሆይ፤ የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ ይፈወስ ዘንድ ክንዱ አልተጠገነም፤ ወይም ሰይፍ መያዝ ይችል ዘንድ እጁ በመቃ አልታሰረም። 22ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነሥቻለሁ፤ ደኅናውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤ ሰይፉም ከእጁ እንዲወድቅ አደርጋለሁ። 23ግብፃውያንን በሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ። 24የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስይዘዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም በፊቱ ክፉኛ እንደ ቈሰለ ሰው ያቃስታል። 25የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ የፈርዖን ክንድ ግን ይዝላል፤ ሰይፌን በባቢሎን ንጉሥ እጅ ሳስይዝ፣ እርሱም ሲነቀንቀው፣ ያኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ። 26በሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”

Copyright information for AmhNASV